ምሥጢረ ሥላሴ ክፍል ሁለት

የአንድነትና ሦስትነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ

ዘፍ 11 እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ  (አንድነቱን)

ዘፍ 126 እግዚአብሔርም አለ ሰውን በመልካችን እንደምሳሌያችን እንፍጠር (ሦስትነቱን)

  • እግዚአብሔርም አለ ሲል አንድነቱን
  • በመልካችን እንደ ምሳሌያችን ሲል ደግሞ ሦስትነቱን
  • አንድም
  • ንግበር  (እንፍጠር) ሲል ደግሞ የሦስትነቱን
  • እንደ አንድ ቃል ንግበር ሲል ደግሞ የአንድነቱን

ዘፍ 322 እግዚአብሔርም አለ እነሆ አዳም መልካምንና ክፉን ለማወቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ

  • እግዚአብሔርም አለ ሲል አንድነቱን   
  • ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ ሲል ደግሞ ሦስትነቱን

ዘፍ 117    እንውረድ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው

  • እንውረድ የሚለው አንድ እግዚአብሔር
  • አንድም
  • እንውረድ የተባሉ ሁለትና ከዚያ በላይ እንዳሉ የሚጠቁም ሲሆን ሦስትነትን ያመለክታል
  • ሥላሴም ያንዱን ቋንቋ አንዱ እንዳይሰማው ወርደን ቋንቋቸውን እንደባልቀው አሉ

ዘፍ 181   የእግዚአብሔር ለአብርሃም ተገለጠለት ካለ በኋላ

  • አብርሃም የተመለከተው ሦስት መሆናቸው እግዚአብሔር አንድነት
  • ሦስት ሰዎች በፊቱ ያያቸው ደግሞ ሦስትነት ነው፡፡
  • ደግሞም አብርሃም በፊትህ ሞገስ አግኝቼ እንደሆነ ባርያህን አትለፈኝ ማለቱ የአንድነቱን ይገልጻል
  • ሦስት መስፈሪያ የተሰለቀ ዱቄት ፈጥነህ አዘጋጅ ለውሺ እንጎቻም አድርጊ አላት
  • ሦስት መስፈሪያ ሦስትነቱ
  • አንድ ሆኖ መጋገሩ ደግሞ አንድነቱን ይገልጻል

ኢሳ 63 አንዱም ለአንዱ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች እያለ ይጮህ ነበር

  • የሠራዊት ጌታ ሲል አንድነቱን
  • ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ብለው ሲያመሰግኑ ሦስትነቱን ተናገሩ ቅዱስ የሚለው ቃል ዝቅ ብሎ ሁለት ከፍ ብሎ አራት አልሆነምና

ኢሳ 4816 ወደ እኔ ቅረቡ ይህንም ስሙ እኔ ከጥንት ጀምሬ በሥውር አልተናገርኩም ከሆነበት ዘመን ጀምሮ እኔ በዚያ ነበርሁ አሁንም ጌታ እግዚአብሔርና መንፈሱ ልከውኛል

  • ይህንን የተናገረው ተላኪ እግዚአብሔር ወልድ ሲሆን
    • እግዚአብሔር አብ ውረድ ተወለድ ብሎ ላከኝ መንፈስ ቅዱስም አዋሐደኝ ሲል አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በየድርሻቸው በሦስትነት ተገልጸዋል
    • ወልድ ተወለደ
    • አብ ወልድን ወለደ መንፈስ ቅዱስን አሰረጸ
    • መንፈስ ቅዱስም ተዋሐደ

ማቴ 316 ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውሃ ወጣ እነሆም ሰማያት ተከፈቱ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ እነሆም ድምጽ ከሰማያት መጥቶ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ

  • በጥምቀት የእግዚአብሔር አንድነት የእግዚአብሔር ሦስትነት ታይቷል
  • አብ በደመና ሆኖ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው በተለየ አካሉ
  • ወልድ ሲጠመቅ በተለየ አካሉ በባሕረ ዮርዳኖስ
  • መንፈስ ቅዱስ በእርግብ አምሳል በተለየ አካሉ

ማቴ 2819 እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ እያጠመቃችሁ  ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማርችኋቸው ደቀ መዛሙርቴ አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ

  • ስታጠምቋቸውም  በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ብላችሁ አጥምቋቸው
  • አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በግልጽ ይታያል

ሉቃ 135 መል አኩም መልሶ እንዲህ አላት መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፤ የልዑል ሃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ካንቹ የሚወለደው ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል

  • የልዑል ሃይል ይጸልልሻል (አብ)
    • ከአንቺ የሚወለደው ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል ( መንፈስ ቅዱስ)
    • መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ይመጣል (መንፈስ ቅዱስ)
    • በግልጥ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስን ያመለክታል፡፡

ዮሐ 728  እንግዲህ ኢየሱስ በመቅደስ ሲያስተምር እኔንም ታውቁኛላችሁ፤ ከወዴት እንደሆንሁ ታውቃላችሁ፤ እኔም በራሴ አልመጣሁም ነገር ግን እናንተ የማታውቁት የላከኝ እውነተኛ ነው እነ ግን ከእርሱ ዘንድ ነኝ እርሱም ልኮኛልና አውቀዋለሁ ቦሎ ጮኸ

  • የላከው   አብ
    • የተላከው  ወልድ (ኢየሱስ ክርስቶስ)
    • ሁኔታው (ማስተማሩ) የመንፈስ ቅዱስ

ሐዋ 314 ከእናንተ ዘንድ ስኖር ይህን ነግሬአችኋለሁ አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል

  • አብ በስሜ የሚልከው   አብ
    • ከእናንተ ጋር ሳለሁ ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ
    • የሚልከው የእውነት መንፈስ ጰራቅሊጦስ፤ መንፈስ

1 ቆሮ 1314  የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሒር ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን አሜን

  • የእግዚአብሔር ፍቅር፤  አብ
  • የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፤ ወልድ
  • የመንፈስ ቅዱስ አንድነት (ሕብረት) መንፈስ ቅዱስ

1 ቆሮ 124  የጸጋም ስጦታ ልዩ ልዩ ነው፤ መንፈስ አንድ ነው፤ አገልግሎትም ልዩ ልዩ ነው ጌታም አንድ ነው፤ አሠራርም ልዩ ልዩ ነው ሁሉን በሁሉ የሚያደርግ እግዚአብሔር አንድ ነው፡፡

  • እግዚአብሔር አንድ ነው፤ የእግዚአብሔር አብ
    • ጌታም አንድ ነው፤ ኢየሱስ ክርስቶስ
    • መንፈስ ቅዱስ አንድ ነው፤ መንፈስ ቅዱስ (ጰራቅሊጦስ)

ኤፌ 44 በመጠራታችሁ በአንድ ተሥፋ እንደ ተጠራችሁ አንድ አካልና አንድ መነስ አለ፤ አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤ ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ፡፡

  • የሁሉ አባት፤ አብ
    • አንድ ጌታ፤ ወልድ (ኢየሱስ ክርስቶስ)
    • አንድ መንፈስ፤ መንፈስ ቅዱስ

ምንች : አንደሮሜዳ – ዶር  ሮዳስ